top of page

የቡርጂ ሕዝብ ባህል፤ ታሪክ እና ምልከታ

ቡርጂ በደቡባዊ የኢትዮዽያ ክፍል የሚኖር ሕዝብ ሲኾን የራሱ የኾነ ባህል፤ ታሪክ፤ ቋንቋ፤ አመለካከት እና የአኗኗርዘይቤ ያለው ሕዝብ ነው። ቡርጂኢትዮጵያብሔር ነው።

ወረዳው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ከሚገኙ 14 ዞኖች አንዱ በሆነው በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን ውስጥ ካሉ 5 ወረዳዎች አንዷ ነች፡፡ -ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በደቡባዊ ምሥራቅ በ5ዲግር 13’ 18’’ እና 5ዲግር 42’ 00” ‹‹ላቲትዩድ መስምርና በ35ዲግር 34’ 2” እና 37ዲግር 58’ 2” ምስራቅ ሎንግትዩድ መሀከል ይገኛል፡፡ የድንበር አዋሳኞች -በምሥራቅ እና በደቡብ ከኦሮሚያ(ቦረና ዞን) ሀገረ ማርያም -በምዕራብ ከኮንሶ ወረዳ -በሰሜን ከአማሮ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡

የወረዳው የቆዳ ስፋት -ጠቅላላ የወረዳው ቆዳ ስፋ 1877.6 ካሬ ኪ.ሜ/187760 ሄክታር ሲሆን የሕዝብ ብዛት 87789 አካባቢ ነው፡፡ -የመስተዳደር መዋቅር በ24 የገጠር ቀበሌያትና ሁለት የከተማ ቀበሌያት አንድ 5ኛ ደረጃ ማዘጋጀ ቤት እና ሦስት ታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች በድምር በ26 ቀበሌያት ተዋቅረዋል፡፡

የአየር ንብረቷን በተመለከተ -አማካይ የዓመታዊ የዝናብ መጠን 801-1000 ሚ.ሜትር፣ አማካይ የሙቀት መጠን 15.1 ዲ.ሴ -27.5 ዲ.ሴ ሲሆን * ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታ ከ810-2852 ሜትር ነው፡፡ የአየር ፀባይ ቆላ 38-40፣ወይና ደጋ 46 እና ደጋ 14 በመሆን ሦስት የአየር ፀባያት ይኖረዋል፡፡በወረዳዋ ጤፍ፣ ቡራ ቡርጂ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ እንሰት፣ ሙዝ፣ ሽምብራ፣ ገብስ፣ ካዛቫ፣ አተር፣ምስር. . . . ወዘተ ይበቅልበታል፡፡

በሀ/ማርያም (ቡሌ-ሆራ) ከሚያልፈው ዋና አስፋልት መንገድ ጀምሮ እስከ ሶያማ ከተማ 61ኪ.ሜ የጠጠርመንገድ፣ ከዲላ እስከ ቡርጂ 159ኪ.ሜ በከፊል አስፋልት በከፊል የጠጠር መንገድ እና ከቡርጂ እስከ ኮንሶ 80 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ተጠቃሚ ነው፡፡ በሌሎችም የልማት መስኮች የወረዳው ዋና ከተማ የ24 ሰዓት የመብራት፣ የአውቶማቲክ ተንቀሳቃሽ (ሞባይል) ስልክ አገልግሎት እና የገጠር ቀበሌያት ጨምሮ በአጠቃላይ 31.5 ንፁሕ የመጠጥ ውኃ አገልግሎ ተጠቃሚና በአሁኑ ጊዜ 6 ቀበሌያት የማብራት ተጠቃሚ ሲሆኑ ሌሎች በቅርብ ጊዜ መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ቡርጂ የራሷ የሆነ መጠሪያ ያላት ስትሆን ቡርጂ Dashate የሚል የራሷ የሆነ ብቸኛ ቋንቋ ባለበት ነች፣ ስለዚህ ቡርጂ የራሷን ማንነትየሚገልፅ ባህል፣ ወግና ሥርዓት ያለት፤ በብሔሩ የሰውን ነገር መንካት አስፀይፊ እንድሆነ የምትመለከት ብሔር ነች ።በመሆኑም ቡርጂ የምትታወቅባት 27 ቀበሌያት ሶያማ 01 ፣ሶያማ 02፣ ሐራወንጄ፣ ትሾ፣ሙሬ፣ ኦቶሞሎ፣ ወርደያ ጉዴ፣ ድንቤቾ፣ ራሌያ ጎቼ፣ ብላ፣ ገራ፣ ዋለያ ጩሉሴ፣ ሐራሌ፣ አበላ ነዴሌ፣ ሐልዳሜ ፣ ላድሼ፣ የበኖ፣ ዳልኦ፣ ገምዮ፣ ክልቾ፣ ሰጎ፣ ለሞ፣ እና ጎማይደ(አዋር) ቀበሌያት ጎበዜ፣ ትንሿ ቀያተ፣በረቅ ና በኔያ ቀበሌያት ስሆኑ ትንሿ ቀያተ በቅርብ በሰገን ዞን ከተማነት ተቀላቅላለች ስለዚህ አጠቃላይ እነዚህ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩት 85% አርሶ አደር ናቸው። በወረዳው የሚመረቱ አብዛኛው የጤፍ ምርትና በቡራ ቡርጄ አማራ በመሆኑ ቡርጂ እስከ ናዝረት አዳማ እና እስከ ናይሮብ ቦንቦሳ ማርሳቤት ድረስ ይታወቃሉ። ሌላው በወረዳው የበቆሎ ፣ የስንዴ፣ የገብስ እህሎች ይመረታሉ። ✍በወረዳችን የሚታወቁ ነገሮች ማራክና ሳቢ መንፈስዎን የሚያድሱበት አይተው በተፈጥሮ የሚደሰቱበት ሌላኛው ከቅርብ ጊዜ የተፈጠረው የኬላሌ ሐይቅ፣ የሚንሞና ዋሻ፣ የወዮ ደን እና የኤርዶያ ተራራ በከፍተኛው በወረዳችን የሚታወቁ በመሆናቸው ቀጣይ ላይ እነዚህ መስህቦች ቢለሙ ከፍተኛ ለወረዳው ገቢ ስለሚያስገኝ ወረዳው ጠንክረው ሊሰራበት የሚገባ ሥራ ነው።ስለዚህ ወረዳዋን መታችሁ ጎብኙ መልዕክታችን ነው።

1. በወረዳ ከሚገኙመስህቦች በከፊል ሚና-ሞና ዋሻ

የሚገኝበት ቦታ፡- በቡርጂ ወረዳበየበኖ ቀበሌ ከወረዳው ዋና ከተማ ያለው ርቀት 15 ኪ.ሜትር ከቀበሌው ያለው ርቀት 15 ኪ.ሜትርከቀበሌው በእግር ጉዞ የሚፈጅበት ጊዜ 30 ደቂቃ ሲሆን፤ መስህብነቱ፡- ይህ ዋሻ በወረዳው ካሉት ዋሻዎች በይዜቱ፣ በስፋቱና በግዙፍነቱ ልዩ ከመሆኑም በላይ ከሦስት ትላልቅና ሰፋፊ ኣለቶች አንዱ በሌላኛው ላይ ተነባብሮ ሦስት ክፍል የሠራና ከዘመናዊ ፎቅ ቤት ጋር ተመሳሳይ ይዜት ያለው መሆኑ ነው፡፡ ሌላው አስደናቂና ማራኪ የሚያደርገው ይህ ግዙፍ ባለሦስት ክፍል ዋሻ በሰንሰለታማ ገደል አፋፍ ተንጠልጥሎ ያለ ምንም ድጋፍ መቀመጡ ነው፡፡ ዋሻው ባጠቃላይ በሦስቱ ክፍሎች እስከ 50 ሰዎች የመያዝ አቅም ሲኖረው በአንደኛው ክፍል 8፣ በሁለተኛው ክፍል 5 እና በሦስተኛው ክፍል እስከ 27 ሰዎችን ይይዛል፡፡ ሚንሞናን ሲጎብኙ ከየበኖ እስከ ሐላሜ ያለውን ሰንሰለታማ የመሬት አቀማመጥ በከፊል፣ ማራኪ ሸንተረሮችና የሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ያሉበት ሜዳ እንዲሁም ከቡርጂና ከአማሮ ምዕራብ ክፍል ገባር ወንዞች የዳበረና ሜዳውን ሰንጥቆ የሚጓዘውን በጉማሬና በሌሎች እንስሳት የተካነውን ትልቁን የሠገን ወንዝ የመጎብኘት ዕድል ይኖርዎታል፡፡

2. ከየበኖ እስከሐላሜ ሰንሰለታማ የመሬት አቀማመጥ በከፊል

-ሚገኝበት ቦታ፡- በቡርጂ ወረዳ ከየበኖ እስከ ሐላሜ ቀበሌ ድረስ የሚዘልቅ -ከወረዳዋ ዋና ከተማ ያለው ርቀት 15-30 ኪ.ሜ -ከእያንዳንዱ ቀበሌ ያለው ርቀት 1.2-1.5 ኪ.ሜ፡፡

-መስህብነቱ፡- ተፈጥሮአዊ ይዜትና ከ15-20 ኪ.ሜ ርዝመትያለው ነው፡፡ ከሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ሜዳ ወደ ላይ አሻቅበው ሲጎብኙ ሰንሰለታማው የመሬት አቀማመጡ እጅግ ማራኪ ዓይን የሚሰብና ወጥነት ያለው ከአናት ላይ የማይበላለጥና በእኩል ርቀት ሦስት የተደረደረ መወጣጫ መሰላል የሚመስል እይታ ያለው ነው፡፡ ... ይህን የተፈጥሮ መስህብ ሲጎብኙ ሌሎች እንደ ሚንሞና ዋሻ የሠገን የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት ሜዳ እና የተለያዩ የመልከ ዓምድር አቀማመጦችን የመጎብኘት ሰፊ ዕድል ይኖርዎታል፡፡

3. ዲቃቼ ፏፏቴ

ፏፏቴው የራሱ ታሪክ አለው፡፡ዲቃ/ዲቂ ማጠብ፣ ጓል…የሚል ፍቺ ቢኖረውም ከፏፏቴ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ መታጠብ ቀጥተኛ ገላጭ ነው፡፡ መስህብነቱ፡- በአካባቢው ሸማግሌዎች እንደምነገረው ለግዝረት ዕድሜያቸው የደረሱ ወጣት ወንዶች በእለተ ግርዛት ማልደው ፏፏቴ ይወረዱና ገላቸውን በደንብ ይታጠባሉ ፡፡ይህም ግርዛት የሚሰራው በስለት ስለሆነ ተያይዘው ከሚከሰት ማናቸውም በሽታና ‹‹ልክፍት›› (እንድነሱ) ሁሉንም በመነጻጻት ለመታደግ ሲባል ነው፡፡አሁን ከግንዛቤ መዳበርና ባዕድ አምልኮ ልየታ ደረጃ እያደገ መምጣት ጋር ቢቀርም ተጋቢ ሙሽራዋና ሚዜዎቿ ከአንድ ቀን በፊት በፏፏቴ መታጠብ ግድ ነበር ይላሉ እነዚህም ተራኪዎች፡፡ ኮረዳዎችም እንደ ወንዶች አስተዳደጋቸው‹‹ንጹህ›› ስለነበረ አሁን ደግመው ወግ ማዕረግ ለማየት በመቃረባቸው ከታዳጊነት ወደ እማወራነት መሸጋገሪያ ማሳያው ፏፏቴውን በቅድመ ጋቢቻ መጎብኘት ነው፡፡ከዚህም በኃላ የቤትና ቤተሰብ ሀላፊነትን ከእናቶቻቸው ለመረከብ ብቁ ስለመሆናቸውና እነሱም በተራቸው ለማሰረከብ ትውልዳዊ አደራና ኃላፊትነት የመከወን ተግባር ቃል ኪዳን ነው፡፡ወንዶችም ራሳቸውን አሳችለው መስራትን በመለማመድ የዛሬው ወጣት የነገው አባወራ መሆኑን ራዕይ መሰነቂያ ባህል ያዳብራሉ፡፡

4. ኤርዶያ ተራራ የሚገኝበት ቦታ፡- በቡርጂ ወረዳ በክልቾ ቀበሌ ከዋና ከተማ የሚገኝበት ርቀት 2 ኪ.ሜነው፡፡ መስህብነቱ፡- ይህ ተራራ ሰፊና የተንጣለለ ሜዳ በአናቱ ስላለው የመዝናኛ ሎጅ ለመገንባት ጠቀሜታ አለው፡፡ በሰንበለጥና በደን የተሸፈነ በመሆኑ ለዱር እንስሳት መጠለያነትም ያገለግላል በተጨመሪም ታሪካዊ መስህብነቱ እንደዛሬ መገናኛ በልነበረበት ዘመን የቡርጂና የኮንሶ አጎራባች ብሔረሰቦች በተራራው ጫፍ እሳት በመለኮስ በምልክት መገናኛ መልዕክት ይለዋወጡበት ነበር፡፡

5. ወዮ የተፈጥሮ ደን ወዮ በቡርጂ ወረዳ በዋለያ ቀበሌ ይገኛል፡፡

ከዋና ከተማ ያለው ርቀት 21 ኪ.ሜከቀበሌው ያለው ርቀት 1.5 ኪ.ሜ፡፡ ወዮ በቡርጂብሔረሰብ ነውር፣ ለመተግበር ጾያፍ የሆነ የተከለከለና አሳፋሪ ድርጊት ማለት ነው፡፡ የወዮ ደን ያለበት አካባቢ የሕዝብ አካልና ወገን 3 የነበሩ ጎሳዎችና ሰዎች በበሽታ ተጠቅተው ያለቁበት በመሆኑ ሌሎች ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ጎሣዎች መጠቀም ወይም በይዞታነት መያዝ በነውርነት ስለተፈረጀ ሳይታረስ ለብዙ ጊዜያት በመቆየቱ የተለያየ የዛፍ ዝሪያ ያለበት ደን በቅሎና ለምቶ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ መምጣቱን እነዚህን የተረኩልን ሽማግሌዎች ይመሰክራሉ፡፡ ደኑ በኤሳው (ባህላዊ ባለሥልጣን) አማካይነት ያለ ምንም ክፍያለማህበረሰቡ እንደ ጠያቂው ፍላጎት በህዝብ ተወካዮች አመኔታ ለቤትና ለሌሎች አገልግሎቶች ይውላል፡፡ አሁንም በህብረተሰቡ እየተዳደረና ጥቅም እየሰጠ ይገኛል፡፡ ወዮ የተፈጥሮ ደን ወሎ በሚል ስያሜ ከምኒልክ ወረራ ጋር ተያይዞ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የመጡ ግለሰቦች ከአገራቸው ወሎ ክ/ሀገር አንጻር ስያሜ እንዲኖረው አድርገው እንደሰየሙት በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አባቶችና ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ወዮ የተፈጥሮ ደን ከብዙ ዘመናት ቆይታ የተነሳ የተለያዩ የዛፍ ዓይነቶችና የዱር እንስሳት የሚገኙበትና ለአካባቢው ለተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ ለመስብህነትም የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

6. ሠገን ኬላሌ ሐይቅ የሚገኝበት ቦታ በቡርጅ ወረዳ ክልቾ ቀበሌ ሲሆን ከወረዳ ዋና ከተማ ያለው ርቀት 42ኪ.ሜ ከቡርጅ-ኮንሶ ጠጠር መንገድ ከዋናው መኪና መንገድ 1.5ኪሜ ላይ ይገኛል፡፡

መስህብነቱ ፡-የሐይቅ አቀማመጥበሁለቱ ተራሮች መካከል የተቀመጠ በመሆኑ እይታ የሚማርክ መሆኑ በዋና/በጀልባ/ መዝናናት ለሚፈልግጉ ጎብኚዎች በሐይቁ በመዝናናት መንፈሳቸውን ያድሳሉ የተለያዩ የውሃ አካላትንም በሐይቁ ውሰጥ እየተፈጠሩ ስላሉ ዓሣ፣ አዞና ጉማሬ የመጎብኘት ዕድል ይኖራሉ፡፡ በየሬሾና ጉበለቾ ተራራ ላይ ሎጅ ቢገነባ ሐይቁን ሊጎበኙ ለሚመጡ ቱርስቶች ማረፊያ ከመሆኑም በላይ የተሻለ ኢኮኖሚ የሚያገኙበት ምቹ አጋጣሚ ይገኛሉ፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች በጀልባ ስራና በዓሣ አስገራ ተግባራት ላይ በሥራ ዕድል ፈጠራ በር የሚከፍት ሆኖል፡፡ በውሃ አካላት ላይ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ሆኖል ይቀጥላል ። ሪፖርተር Dambi burji

 
 
 

Recent Posts

See All
Metamorphic Petrology

Chapter -1 Introduction to Metamorphism Chapter -2 Metamorphic Processes Chapter -3 Metamorphic Rocks and Minerals Chapter -4 Metamorphic...

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page